የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው የትንሳኤን በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 26/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው የትንሳኤን በዓል በማስመልከት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ያለፉት የፆምና የፀሎት ጊዜያት በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ መንፈሳዊ ሕይወትን በማደስ ፈሪሃ ፈጣሪን የተላበሰ ስብዕናና ሞራላዊ እሴትን ለማጠናከር ጉልህ ሚና የተጫወቱ ናቸዉ ብለዋል።
በየእምነቶቻችን አስተምህሮዎችና ድንጋጌዎች መሠረት የምናከናዉናቸዉ ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ዉስጣዊና ዉጫዊ ሠላምን በማጎናፀፍ የእርስበርስ ትስስራችን በፍቅር፣ በመከባበርና በመቻቻል ላይ እንዲመሠረትና እንዲጠናከር ድልድይ ሆነዉ የሚያገለግሉ ናቸዉ ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል።
በፆሙ ጊዜያት ያጎለበትናቸዉ መልካም ተግባራት የአብሮነትን ድልድይ የሚያጠናክሩ፣ መልካምነትን የሚያላብሱ፣ የመተባበርና የመቻቻል ሠንሰለትን የሚያጎለብቱ በመሆናቸዉ የዘወትር የምግባርና የተግባር መርሆዎቻችን ሆነዉ እንዲቀጥሉ ጥረት ማድረግ ይኖርብናል ብለዋል።
በዓሉ የሐሴት፣ የበረከትና የሠላም እንዲሆንላችሁ በድጋሚ እመኛለሁ ሲሉ ነው ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው መጥቀሳቸውን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያሳያል።

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ