ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 26/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የትንሳኤ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያለውን ፅኑ ፍቅር በመስቀል ላይ ያሳየበት እንዲሁም ይቅርታና ምህረትን ለሰው ልጆች የሰጠበት የጥልና የመለያየት ግድግዳን አፍርሶ የሰውን ልጅ የታደገበት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩት መንፈሳዊ በዓላት አንዱ ነው ሲሉም ተናግረዋል በመልዕክታቸዉ።
ይህ የትንሳዔ በዓል መታዘዝን፣ይቅርታንና ምህረትን እንዲሁም አንዱ ለሌላው መተሳሰብ እንዳለበት የሚያስተምረን ሲሆን መረዳዳትንና መጠያየቅን ከተለመደው ባህል ባለፈ በፍጹም መንፈሳዊነት ስሜት በጎዳና ላይ የወደቁትን በማሰብ፣በህግ ጥላ ስር ያሉትን በመጠየቅ፣ታመዉ የተኙትን በማጽናናትና ካለን ላይ በማካፈል በአብሮነት ትንሳኤውን የምናከብርበት በዓል ሊሆን ይገባልም ስሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በደል ተላልፎ በመሰጠት የሰውን ልጆች ከጨለማ ወደ ብርሃን ነጻ ለማውጣት ዋጋ የከፈለበት በመሆኑ እኛም አቅሜ ደካሞችን በመርዳትና ካለን በማካፈል ና ለወገኖቻችን በመድረስ ና በመተሳሰብ በዓሉን እንዲናከብር ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የትንሳኤ በዓል ለክልላችና ለሀገራችንና ህዝቦች እንዲሁን ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን የሰላም፣የበረከት፣ የመተሳሰብና የፍቅር እንዲሆንም መመኘታቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ