የትንሳኤ በአልን ምክንያት በማድረግ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ማእድ አጋሩ
ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 24/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሀዋሳ ከተማ ለሚገኙ ከ300 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማዎችና አረጋዊያን ነው የትንሣኤ በአልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ ያጋሩት፡፡
የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነትና ማሕበራዊ ችግር በመተጋገዝና በመተባበር መቅረፍ እደሚገባ የገለጹት ርእሰ መስተዳደሩ፥ ባለፋት 4ና 5 አመታት የአቅመ ደካማዎችን ማህበራዊ ኃላፊነት በመጋራት፥ ቤታቸውን በማደስና በመስራት፣ ማእድ በማጋራት መርሀ ግብር ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል፡፡
የሲዳማ ክልል ወጣቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ኢሳያስ በበኩላቸው፥ በዚህ ማእድ ማጋራ ፕሮግራም ላይ የተሳተፉ አረጋውያን አቅመ ደካማ እንዲሁም ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የተደረገ መሆኑን ጠቁመው፥ እንደ ክልል በአሉን ምክንያት በማድረግ ከ15 ሺህ በላይ ለሆኑ ድጋፍን ለሚሹ ወገኖች ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው አሁን ላይ ከ300 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካማዎች ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚሁ ወቅት በዓሉን ለሚያከብሩ መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳቹ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ቤተልሔም ለገሰ

More Stories
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፍትህና የጸጥታ ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
ከአየር ንብረት ተፅዕኖ ጋር እየተስተዋሉ ያሉትን ችግሮች ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን አስታወቀ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ጀመረ