ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለተከናወኑት የ’ገበታ ለሀገር’ ፕሮጀክቶች አንድ ሌላ ምዕራፍ ተከናውኗል
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀ መርሃ ግብር የ’ገበታ ለሀገር’ ፕሮጀክቶቹን ለአማራ፣ ለኦሮሚያ እና ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስረክቧል።
በተጨማሪም በገበታ ለሀገር የተገነቡ ሎጆችን ስራ የማስኬድ ተግባርን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስካይ ላይት ሆቴል ተቋሙ በኩል እንዲወጣ የስምምነት ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።
ከአራቱ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክቶች ሶስቱ (ሃላላ ኬላ ሎጅ፣ ጨበራ ጩርጩራ የዝሆን ዳና ሎጅ እና ወንጪ ኢኮ ሎጅ) በቅርቡ መመረቃቸው የሚታወሰ ሲሆን የጎርጎራ ፕሮጀክት ስራም በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
በጠቅላይ ሚኒስሩ ከፍተኛ ትኩረት እና አመራር የተከናወነው የ’ገበታ ለሀገር’ ስራ የብሔራዊው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አንዱ ማዕዘን የሆነውን ቱሪዝምን የማሳደግ አላማ ያለው ነው።
እነዚህ ፕሮጀክቶች በመጀመሪያው ፋይናንስ የማሰባሰብ ምዕራፍ የኅብረተሰቡን ድጋፍ በሰፊው ያሰባሰቡ፣ በግንባታቸው ምዕራፍ ግዙፍ የስራ ዕድል የፈጠሩ ብሎም ታላላቅ የመሰረተ ልማት ስራዎች እንዲከናወን በር የከፈቱ ናቸው።
በፈጠራ የተሞላ የፕሮጀክት ስራ እና አስተዳደር እና ፈጣን አፈፃፀም ምን ሊመስል እንደሚችል ማሳያም ሆነዋል።
ቀጣይ የስራ ማስኬድ እና ማስተዳደር ተግባሩ ለብሔራዊ ሰንደቅ ተሸካሚው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሃላፊነት መሰጠቱም የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ከማስቻሉም ባለፈ ለአለምአቀፍ የቱሪዝም መዳረሻነት ትውውቅ ከፍ ያለ ዕድል ይፈጥራል።
ምንጭ፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ