የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ የመንግስት ተቋማት ለተለያዩ አካላት ድጋፍ አበረከተ

የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ የመንግስት ተቋማት ለተለያዩ አካላት ድጋፍ አበረከተ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 23/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ከክልሉ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮና ከኣሪ ዞን ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ጋር በመተባበር የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋውያን ፣ለአካል ጉዳተኞችና ተጋላጭ ለሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ቁሳቁስና የተለያዩ ድጋፎችን አበረከተ።

በድጋፍ ቦታ የተገኙት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ የሀገር ባለውለታ የሆኑ አረጋዊያንን መደገፍ ትልቅ ክብር ነው።

ዞኑ ከዚህ በፊት በበዓላትም ይሁን ከአዘቦት ቀን ውጭ ድጋፍ ለሚሹ አካላት ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው ትንሳኤ በዓልን ምክንያት ተደርጎ የተረገው ድጋፍ አንዱ ነው፤ የዞኑ አስተዳደር መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል አቶ አብርሃም ።

2016 ዓ/ም ትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ የተደረገላቸው አካላትን እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ በዓል አደረሰን አደረሳችሁ ምኞት የገለፁት አቶ አብርሃም ለመላው የዞንና ኢትዮጵያዊያን መልካም በዓል ይሁንልን ብለዋል

የደቡብ ኢትዮጵያዊ ክልል ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዋኖ ዋሎሌ በጎ ተግባር ለራስ ክብር በመሆኑ ለሀገር ባለውለታ የከፈሉ አካላት ሳይቸገሩ በዓሉ እንዲያሳልፉ ቢሮ ከሌሎች ቢሮዎች ጋር በመቀናጀት ከ2 መቶ በላይ ለሚሆኑ አካላት ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።

ሁሉም ሰው ይህንን በጎ ሥራ በማካሄድ እንደሀገር በተለያየ ምክንያት የተቸገሩትን ልንረዳ ይገባል ሲሉም ገልፀዋል ዶ/ር ዋኖ።

ለመላው ኢትዮጵያውያን በዓሉ የሠላም እንዲሆንም ሀለፊው ተመኝተዋል።

የክልሉ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ጉዳይ ሀላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ ቢሮው የትንሣኤ በዓልን ምክንት በማድረግ የተለያዩ የአልባሳት ድጋፎችን ማበርከቱን ገልፀዋል።

አቅመ ደካሞችን ማገዝ፣መርዳትና ችግራቸውን ማድመጥ የአንድ ወቅት ተግባር ብቻ ሳይሆን የሁልጊዜ ተደርጎ ልቆጠር ይገባል ያሉት ወ/ሮ ካሰች እንደሀገር ተግባሩ በጠቅላይ ሚኒስትር አነሳሽነት በመላው የኢትዮጵያ ክፍል በተለያየ መልኩ እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል።

እንኳን ለ2016 ዓ/ም ለትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሰን መልዕክት አስተላልፈው በዓሉ የሠላም ፣የፍቅርና የመረዳዳት እንዲሆን የቢሮ ሀላፊዋ ተመኝተዋል።

ድጋፉን ያገኙ አካላትም በዕድሜ መግፋትና በተለያየ ምክንያት አካለ ጎደለው ሆነው አቅም አተው ተቸግረው እየኖሩ ሳሉ በዓሉን እንደማንኛውም ሰው ያለምንም ችግር በዓሉን እንዲናሳልፍ የተደረገልን ድጋፍ በመሆኑ ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል።

በጎና ቀና ሐሳብ ይዘው ይህንን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ፈጣሪ ዕድሜያቸውንና ጤናቸውን ይጠብቅላቸው ብለው ያመሰገኑት ድጋፍ ተረካቢዎች ለዓመቱ ፈጣሪ በሠላም እንዲያደርሰን እንማፀናለን ብለዋል።

በክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አማካኝነት በዓሉን ምክንያት በማድረግ በክልሉ ስር በተለያዩ ቦታዎች መሰል ድጋፎች እንደሚደረጉ ተገልጿል ።

ዘጋቢ: ተመስገን አበራ-ከጃንካ ጣቢያችን