ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 22/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሴት ተማሪዎችን አቅም በማጎልበት በሀገር አቀፍ ምዘና ላይ የተሻለ ዉጤት እንዲያስመዘግቡ ለማስቻል በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የቡታጅራ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገለፀ።
አላማቸው ከግብ እንዲደርስ ትምህርት ቤቱ እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ እና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የትምህርት ቤቱ ሴት ተማሪዎች ተናግረዋል።
ተማሪ ማህሌት ጌቱ እና ሄዋን ደረጀ የቡታጅራ ከተማ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ናቸው።
ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በብቃት ተከታትለው ጥሩ ዉጤት ለማስስመዘግብ እና አላማቸው ከግብ እንዲደርስ ትምህርት ቤቱ እያደረገላቸው ያለው ድጋፍ እና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
መምህራኖቻቸው ሴት ተማሪዎችን ቲቶሪያል በመጥራትና የተለያዩ ጥያቄዎችን በበማሰራት እገዛ እንደሚያደርጉላቸው አስረድተዋል፡፡
ይህንን ማድረጋቸዉ በፈተናው ላይ በስነ ልቦና ዝግጁ ሆነው ለመቅረብ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡
መምህርት አዲስ አለም ነጋ፣ መምህር ደመላሽ አለሙ እና መምህር ሰለሞን ዮናስ በትምህርት ቤቱ ዉስጥ ሲያስተምሩ አግኝተን ያነጋገርናቸዉ መምህራን ናቸዉ፡፡
በሰጡት አስተያየትትም ሴቶችን ማስተማር ህብረተሰቡን እንደማስተማር ይቆጠራል በማለት ሴት ተማሪዎችን በዉጤት ብቁ ለማድረግ መምህራን ከተማሪዎች ጋር ጥብቅ ቁርኝት ሊኖራቸዉ ይገባል።
በተመሳሳይ ሁኔታ ተማሪዎችም ለመምህራን ግልጽ በመሆን በትጋት መማር አለባቸዉ ብለዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ ለሴት ተማሪዎች የቲቶሪያል ድጋፍ እና አቅም ለሌላቸዉ የንጽህና መጠበቂያን ጨምሮ የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም የማረፊያ ክፍል በማዘጋጀት ምቹ ሁኔታን አመቻችቷል ያሉት የቡታጅራ ከተማ ከፍተኛ 2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ሹምበዛ ታዬ ሲሆኑ ድጋፍና ክትትል ስያደርጉም ከወላጆች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መሆኑን ገልጸዋል።
በጊቢዉ የሚገኙት ሴት ተማሪዎች ክፍል ውስጥ ጥሩ ዉጤት እንዳላቸዉ የተናገሩት ሀላፊዉ ይህንን ዉጤት ወደ ሀገር አቀፍ ፈተና ለመለወጥ በትጋት እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡
በከተማዉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ላሉ ሴት ተማሪዎች የስነ ልቦናን አገልግሎትን ጨምሮ በተለያየ መንገድ ድጋፍ እያደረግን ነዉ ያሉት የቡታጂራ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስርዓተ ፆታ ባለሙያ አቶ ኢብራሂም ናስር ናቸዉ፡፡
ከተማሪዎቹ ጋር በየ 15 ቀኑ ዉይይት በማድረግ ለአቅመ ደካማዎች የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን በመግለጽ የመስጠት ቀን በሚል የደንብ ልብስ የማሰባሰብ ስራ ይሰራልም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ረድኤት እግዜሩ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ