በወረዳው የመጣውን አንፃራዊ ሰላም ለማጽናት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የሸኮ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ

በወረዳው የመጣውን አንፃራዊ ሰላም ለማጽናት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የሸኮ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ

በወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት በማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት ላይ የተደራጁና የሰለጠኑ አባላት የምረቃ ስነ ስርዓትም ተካሂዷል።

ባለፉት ሶስት ዓመታት በፀጥታ ችግር ውስጥ የቆየው የሸኮ ወረዳ ህብርተሰቡ በጋራ ባደረጉት ጥረት ወደ አንፃራዊ ሰላም መምጣቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ርብርብ ማደረግ እንዳለበት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሪ ጉርሙ ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓት ወረዳው ከፀጥታ ችግር ተላቆ ወደ ልማት መመለሱን ተናግረው ይህ እንዳይደናቀፍ ሁሉም ባለበት አካባቢ የራሱን ሰላም በማስጠበቅ ሚናቸውን እንዲወጡም አቶ አሪ አስገንዝበዋል።

በአካባቢው የተፈጠረውን የፀጥታ ችግሮች መነሻ በማድረግ ዝርፊያ፣ ንጥቂያና የተለያዩ ወንጀሎች ሲፈፀሙ እንደቆየ አስታውሰው፤ የፀጥታ አካላት፣ ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት ሰላም መስፈኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ዶክተር ካሳ ተናግረዋል።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው በወረዳው ሰላም መምጣቱን ገልጸው ይህንን ዘላቂ ማድረግ እንደሚገባ አንስተዋል።

የሸኮ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት በ24ቱም ቀበሌያት በ299 መንደር በማህበረሰብ ደህንነት ፓትሮል ቅኝት ላይ የተደራጁ አባላት ምረቃትም ተካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፖሊስ አበላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን