የሐዘን መግለጫ
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በወይዘሮ አለሚቱ አሰፋ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሐዘን ገለፀ።
ወይዘሮ አለሚቱ በክልሉ ጋሞ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊነትን ጨምሮ በዞኑ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች ለረዥም አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ህዝብን አገልግለዋል።
ወይዘሮ አለሚቱ ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ የጋሞ ዞን ገረሴ ቦንኬ ምርጫ ክልል ህዝብን በመወከል፤ በኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በመሆን ሲያገለግሉ ነበር፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በወይዘሮ አለሚቱ አሰፋ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለፀ፤ ለቤተሰባቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሥራ ባልደረቦቻቸው መጽናናትን ይመኛል፡፡

More Stories
የክልሉ ሕዝቦች ሰላምና አንድነት እንዲጎለብት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ገለጹ
ብሔራዊ መግባባት የሰፈነባትን ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ ሀገራዊ ምክክሩ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገለጸ
የኮንታ ዞን ም/ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ ሥራ ዘመን 26ኛው መደበኛ ጉባኤው ተጠናቀቀ