የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ተገለጸ

የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ተገለጸ

በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ አንድ መፅሀፍ ለአንድ ተማሪ በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ሚጁ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት ብቁና የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋ ለማፍራት አንድ መፅሀፍ ለአንድ ተማሪ ተደራሽ በማድረግ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

የይርጋጨፌ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍቅሩ ጠገኖ የትምህርት ስብራትን ለመጠገን የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሀፍትን ሟሟላት ወሳኝ በመሆኑ አዲሱን የስርዓት ትምህርት መፅሀፍ በሟሟላት ችግሩን መፍታት መቻል እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

በ2015 ዓ.ም በወረዳው የ8ኛና 12ኛ ክፍል ውጤት ዝቅተኛ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት የትምህርት አመራር አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

የወረዳው አስተዳደር በመድረኩ በተካሄደው የገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ አንድ የባዮሎጂ መፅሀፍ በ1 ሚሊየን ብር የገዛ ሲሆን በመድረኩ በአጠቃላይ 1ሚሊየን 421 ሺህ 875ብር መሰብሰብ ተችሏል ።

ዘጋቢ፡ ፅጌ ደምሴ ከይርጋጨፌ ጣቢያችን