የሴቶችና ህፃናትን ጥቃት መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ: ሚያዚያ 10/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ተባለ።
የአሪ ዞን ሴቶችና ህፃናት መምሪያ ከፍትህ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር በሴቶችና ህፃናት በሚፈፀሙ ጥቃቶች ላይ ምክክር አድርገዋል።
መድረኩን በንግግር የከፌቱት የኣሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘረፍ ኃላፊና የዞኑ መንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ኢያሱ ዘርፉ በሴቶችና ህፃናት ላይ የምደርሰውን የትኛዉንም ጥቃት ለመከላከል እንዲያስችል የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ከፍትሕ አካላት ጋር በተቀናጀ ሁኔታ ሊሰራ ይገባል ብለዋል ፡፡
የኣሪ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ሲስተር ርብቃ አለማየዉ እንደገለጹት የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ የሴቶችና ህፃናት ተጋላጭነትን በመቀነስ ተጠቃሚነትና ተሳትፏቸውን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ዘጋቢ: ሁሴን ዓለሙ- ከጂንካ ቅርንጫፍ

More Stories
የክልሉ ሕዝቦች ሰላምና አንድነት እንዲጎለብት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ገለጹ
ብሔራዊ መግባባት የሰፈነባትን ሀገር ለትውልድ ለማስረከብ ሀገራዊ ምክክሩ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑ ተገለጸ
የኮንታ ዞን ም/ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ ሥራ ዘመን 26ኛው መደበኛ ጉባኤው ተጠናቀቀ