ከ16 ሚሊዮን በላይ የቡና ችግኞች በክረምቱ ወራት ለመትከል መዘጋጀቱን የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ አስታወቀ

የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ሥራ መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ እንደገለፁት በያዝነው የክረምት ወራት ከ16 ሚሊዮን 632 ሺህ በላይ የቡና ችግኞች ለመትከል ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

ቡና የዞኑ ትልቁ ኢኮኖሚና የገቢ ምንጭ በመሆኑ ለአርሶ አደር ብቻ የሚተው እንዳልሆነና በተሻሻለ የቡና ዝሪያዎች ማሳ እንዲሸፈን በማደረግ በሁሉም ወረዳዎች ከ16 ሚሊዮን በላይ ጉድጓዶች መዘጋጀቱን ኃላፊው ተናግረዋል።

የሚተከሉ የቡና ችግኞች በመንግስት ተቋማትና በልማታዊ ባለሀብቶች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በዞን 157 ሺህ 592 ሄክታር ማሳ በቡና በቡና የተሸፈነ መሆኑን ተናግረው ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ ከፍ ያለ ምርት የሚያስገኝ ሥራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ዘጋቢ፦ አብዲሳ ዮናስ- ከሚዛን ጣቢያችን