በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአከራይ ተከራይ የቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት አስተባባሪ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ ስንታየሁ ወልደሚካኤል ምክክር ያስፈለገው በአዋጁ አተገባበር ዙርያ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ብለዋል፡፡
የቤት ፍላጎትን ለማሳካት አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ መንግስት ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ አማራጮችን አቅርቧል።
በማህበር በማደራጀት የመኖርያ ቤት ፍላጎትን ለማሟላት ተሞክሯል ያሉት ሃላፊው ይሄ በቂ ባለመሆኑ የአከራይ ተከራይ ግንኙነትን በአዋጅ አስደግፎ ማስተዳደር ማስፈለጉን አንስተዋል።
አዲሱ አዋጅ የተረጋጋ የመኖሪያ ቤት ኪራይ እንዲኖር የሚያስችል እንደሆነ ሃላፊው አብራርተዋል።
ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪና በመሀል ውል ማቋረጥን አዋጁ ይከለክላል።
አዋጁ በክልሉ ስድስት የማዕከል ከተሞች ላይ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።
ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ