ባለፋት 10 ቀናት 4 የሱፐርቪዥን ቡድኖችን በማዋቀር በሁሉም ዞኖች ያሰማራው የማህበራዊ ክላስተር የታዩ መልካም ጎኖችንና ክፍተቶችን የሚገመግም የግብረ መልስ መድረክ ነው በወራቤ ከተማ እያካሄደ ያለው።
በሁሉም ዞንና ልዩ ወረዳዎች ቅኝት ያደረገው የሱፐርቪዥን ቡድኑ በጤና በትምህርት በሳይንስና ቴክኖሎጂ በፐብሊክ ሰርቪስ እንዲሁም በሴቶችና ህፃናት ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን ገምግሟል።
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የትምህርት ቢሮ ኃላፊውና የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪው አቶ አንተነህ ፈቃዱ የተመራው የግብረ መልስ መድረክ ክልሉ ሞዴል ሆኖ እንዲወጣ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ እየመከረ ነው።
በሁሉም ዘርፎች የሚታዩ ክፍተቶችን በመፍታት ተሞክሮዎችን ደግሞ ወደ ሁሉም አካባቢዎች በማስፋት በቀጣይ ሁለንተናው ለውጥ ለማምጣት በቅንጅት መሰራት እንዳለበትም ተመላክቷል።
ዘጋቢ : ባዬ በልስቲ
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ