በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ለደረጃ “ሀ” እና “ለ” ግብር ከፋዮች በሂሳብ መዝገብ አያያዝ እና በደረሰኝ አጠቃቀም ላይ የተዘጋጀ የክህሎት ሥልጠና በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ተሰጥቷል
በግብይት ስርዓቱ ላይ ደረሰኝ አለመስጠት በስፋት የሚስተዋል ችግር መሆኑ በዉይይቱ ተመላክቷል፡፡
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊና የገቢ ጥናት፣ የታክስ ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ምትኩ፤ ግብር ከፋዩ ህብረተሰብ የታክስ ሕጎችና ደንቦችን በተገቢው ተገንዝቦ መብቱንና ግዴታውን አውቆ አንዲፈጽምና ወቅቱን የጠበቀ ግብር እንዲከፍል ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል::
የታክስ ሕግ ተገዥነት ጎልብቶና የሚሰበሰበው ገቢ አድጎ ለሀገር ልማትና እድገት እንዲውል የንግዱ ማህበረሰብ የበኩሉን መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።
የጎፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ተባበር ፍቅሩ በበኩላቸው ገቢ በአግባቡ ባለመሰብሰብ ከእቅድ በታች እየሆነ መምጣቱን አንሰተው በቀጣይ የግብይት ሥርዓቱ ደረሰኝ በማይዙ አካላት ላይ አሰተማሪ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ህገ-ውጥ ደረሰኝ አቅርቦትና በቫት መዝገባ የሚሰተዋሉ ችግሮችን አንስተዋል።
ከንግዱ ማህበረሰብ ለተነሱ ሀሳቦች የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትል ሀላፊና የታክስ ህጎች ማስከበር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጻነት አካለወልድ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ከተማዋ ፅዱና ውብ እንድትሆን የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ ነው – የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በቋሚነት የሚደገፉበት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቡርጂ ዞን አስተዳደር አስታወቀ
“አንድ ሰው ወደዚህች ምድር ሲመጣ እንዲሰራ የተፈቀደለትና የሚጠበቅበት ነገር አለ” – ታደሰ ገብሬ /ጃክሰን/