ሀዋሳ፡ ሚያዚያ 04/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአከባቢ ጥበቃ ተግባር ለደን ህልውና መጠበቅ እና ለሁሉ አቀፍ ለውጥ ያለው አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን የኣሪ ዞን ደንና አከባቢ ጥበቃ ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡
በአከባቢ ጥበቃ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስችል የባለድርሻ አካላት የጋራ ምክክር መድረክ በባካ ዳውላ ኣሪ ወረዳ ተካሂዷል፡፡
የኣሪ ዞን ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደምሴ ላልሲ እንደገለጹት ደንን በህገወጥ መንገድ መጠቀም በአዋጅ ቁጥር 10/65/2005 ከአምስት እስከ ሃያ አመት የሚደርስ የእስራት ቅጣት የሚጥል ስለሆነ ማህበረሰቡ ቁጥጥር በማድረግ የደንን ህልውና ለመታደግ ከህግ አካላት ጎን እንዲቆሙ አሳስበዋል፡፡
የባካ ዳውላ አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ባሊ በበኩላቸው ምርትና ምርታማነት ለመጨመር የአከባቢ ደህንነት ለመጠበቅ፣ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋን ለመቀነስ ደን ላይ ማህበረሰቡ በቁርጠኝነት ሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡
ለደን ውድመት መሠረታዊ ምክንያቱ ከደን የሚገኘው ጥቅማጥቅም መሆኑን የሚገልፁት የባካዳውላ ኣሪ ወረዳ ፍትህ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ልሳኑ አስፈፃሚ አካላት ደኑን ወደነበረበት ለመመለስ በትኩረት እንዲሠሩም ጠይቀዋል፡፡
እየጠፋ ያለውን የደን ሀብት በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ ምቹ ስነምህዳር ያላትን መሬት ለማስረከብ ይሠራል ያሉት ደግሞ የወረዳው አከባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ቁጥጥር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስፋው ደቦጭ ናቸው፡፡
በመድረኩ የተሳተፉ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ባለድርሻ አካላት ከአካባቢ ጥበቃ የሚገኘውን ሁለንተናዊ ጥቅም ለማረጋገጥ የድርሻቸውን እንደሚወጡም ገልፀዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ