ሀዋሳ: ሚያዝያ 02/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የኢድ አልፈጥር በዓልን በፍቅርና በመረዳዳት ማክበር እንደሚገባ የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱሽኩር አብዱልቃድር ተናገሩ::
1ሺ 445ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሀዋሳ ከተማ ሚሊኒየም አደባባይ ተከብሯል::
በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱሽኩር አብዱልቃድር፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ አንድነቱን ይበልጥ የሚያጠናክርበት በዓል ነው ብለዋል::
በዚሁ ወቅት በአካባቢያችን ያሉ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ከሁሉም ጋር በፍቅር ማሳለፍ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት::
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ

More Stories
አቶ ይሁን አሰፋ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሾሙ
አቶ መብራቴ ወልደማርያ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በመሆን ተሾሙ
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ያስገነባቸውን 100 መኖሪያ ቤቶችን ለኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች በይፋ አስተላለፈ