ሕዝበ ሙስልሙ ለሀገር ሰላም በማሰብና ለሰው ልጆች እዝነትን በማሳየት ሀይማኖታዊ ግደታውን ሊወጣ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ መሀመድ ጅብሪል ጥሪ አቀረቡ
1 ሺህ 4 መቶ 45ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነው።
ለ30 ተከታታይ ቀናት ሲከናወን የቆየው የረመዳን ጾም ዛሬ በአደባባይ ላይ በሚደረገው ሰላዓትና በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ ነው።
በዚህ ስነ ስርአት ላይ የተገኙት የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ መሀመድ ጅብሪል የረመዳን ጾም የተሳካና በርካታ መንፈሳዊ ተግባራት የተከናወኑበት ነበር ብለዋል።
ህዝበ ሙስልሙም በዓሉን በሚያከብርበት ወቅት የተለመደውን የመረዳዳት፣ የመጠያየቅና መልካም የጉርብትና እሴቶችን በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ሰላም ለእምነት መጠናከርና ለልማት ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ያሉት ሼህ መሀመድ ሁሉም የአካባቢውንና የሀገሩን ሰላምና ፀጥታ መጠበቅ አለበትም ብለዋል።
በመጨረሻም በመላው ዓለም ለሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ኢድ ሙባረክ ሲሉ ፕሬዚዳንቱ የመልካም ምኞት መልዕክታቸዉን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡ አሳምነው አትርሳው – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
ፈጣንና ቀልጣፋ መረጃን ተጀራሽ በማድረግ የመንግስትና የማህበረሰቡን ተግባቦት ይበልጥ ለማጠናከር የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የጎላ መሆኑ ተጠቆመ
ሀገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው
በ17 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሞሪንጋ ጂን ባንክ ለማቋቋም ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ