በረመዳን ፆም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአላህን (ሱወ) ትዕዛዝ እንዳይጥሱ እራሳቸውን በመንፈሳዊ ሥርአት የሚያስገዙበት ብቻ ሳይሆን ሰለምን፣ ፍቅርንና ትህትናን አጥብቀው የሚተገብሩበት፣ መረዳዳትና መተጋገዝ አዘውትረው የሚፈፀሙበትና ነፍስና ስጋ ለቅድስና የሚያስገዙበት ወር ነው – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ

በረመዳን ፆም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአላህን (ሱወ) ትዕዛዝ እንዳይጥሱ እራሳቸውን በመንፈሳዊ ሥርአት የሚያስገዙበት ብቻ ሳይሆን ሰለምን፣ ፍቅርንና ትህትናን አጥብቀው የሚተገብሩበት፣ መረዳዳትና መተጋገዝ አዘውትረው የሚፈፀሙበትና ነፍስና ስጋ ለቅድስና የሚያስገዙበት ወር ነው – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 01/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ)በረመዳን ፆም ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአላህን (ሱወ) ትዕዛዝ እንዳይጥሱ እራሳቸውን በመንፈሳዊ ሥርአት የሚያስገዙበት ብቻ ሳይሆን ሰለምን፣ ፍቅርንና ትህትናን አጥብቀው የሚተገብሩበት፣ መረዳዳትና መተጋገዝ አዘውትረው የሚፈፀሙበትና ነፍስና ስጋ ለቅድስና የሚያስገዙበት ወር መሆኑን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ለመላው የእስልምና ኃይማኖት ተከታዮች አንኳን 1445ኛው ለዒድ አልፈጥር በዓል በሰለም አደረሳችሁ ሲሉ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በተባረከው በረመዳን ወር የሙስሊሙ ማህበረሰብ የፅድቅ ሥራ የሚሰራበት የአላህ (ሱወ) የጀነት በሮች የሚከፈቱበት፤ ሰይጣን የሚታሰርበት ቅዱስ ወር ነው ያሉ ሲሆን፣

የረመዳን ፆም የሀገራችንና የክልላችን የሙስሊሙ ማህበረሰቦች ራሳችሁን ወደ አላህ (ሱወ) በቅድስና አቅርባችሁና አስገዝታችሁ የፆሙን ወር በንፅህና ፈፅማችሁ ለዛሬው ኢድ አልፈጥር በዓል በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

በረመዳን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከኃጢያት የሚሸሽበት፤ ከአሉባልታና ከሐሜት ራሱን የሚገታበት፤ ተንኮልንና ንፉግነትን ተጠይፈው ለሌሎች በደግነት እጁን የሚዘረጋበት ቅዱስ ወር ሲሆን፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የአላህን (ሱወ) ትዕዛዝ እንዳይጥስ ራሱን በመንፈሳዊ ሥርአት የሚያስገዛበት የተቸገሩትን በመርዳት ልግስናውንና ፍቅርን የሚገልፅበት ወርም ነው ብለዋል።

በመሆኑም የሀገራችንና የክልላችን ሙስሊሙ ማህበረሰብ በፆም ወራት በሰደቃ ሰዎችን በገንዘብና በቁስ በመርዳት፥ በጉልበትና በእውቀት በማገልገል፤ በዘካ ዘልፈጥር መንፈሳዊ ስርዓት የተቸገሩትን ወገኖቻችሁን በማብላትና በማጠጣት የአላሃን (ሱወ) ቅዱስ ትዕዛዝ የፈፀማችሁበት ወቅት በመሆኑ ልትመሰገኑ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ቀጥለውም የሀገራችንና የክልላችን ሙስሊም ማህበረሰቦች ያላችሁ ለሌላቸው በማካፈላችሁ፤ የተቸገሩትን በመርዳታችሁ፤ አቅመ ደካማ የሆኑትን በመደገፋችሁ ላለፉት ቅዱስ የፆም ቀናቶች ቅዱስ የሆነውን ኃይማኖታዊ ስርዓት ፈፅማችኋልና በእኔና በመላው በክልል ህዝብ ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

በቅዱስ ቁርአን ነብዩ መሐመድ (ሰዐወ) ከፈጣሪ አላህ (ሱወ) ተቀብለው ቁርአን በመቅራት ነብስንና ስጋን በመልካም ስራዎች በማስገዛት ከአላህ ምንዳን እንደተቀበሉት ሁሉ የክልላችንና የሀገራችን ሙስሊሞች አላህ (ሱወ) ከማይፈቅደው ከዘርና፥ ከኃይማኖትና ፅንፈኝነት እራሳችሁን አርቃችሁ በኢትዮያዊ ጨዋነት ለሀገራችሁ ብልፅግና የራሳችሁን ሚና እንድትጫወቱ አደራ ለማለት እፈልጋለሁ በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በረመዳን ወቅት የነበረው መተዛዘን፣ የመተጋገዝና የመረዳዳት እሴቶችን ከረመዳን በኋላም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

በድጋሚ አንኳን 1445ኛውን ለዒድ-አልፈጥር በዓል በሰለም አደረሳችሁ!

አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር።