ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ያሳያቸውን የበጎነት እሴቶችን በቀጣይ በመደበኛ ተግባራቸው አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል – አቶ ፀጋዬ ማሞ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞ ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች ለ1 ሺህ 445ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በረመዳን ወቅት ያሳየውን አብሮነት በማጠናከር አቅመ ደካሞችን በማገዝና በመንከባከብ፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ በዓሉን ማክበር እንዳለባቸውም ገልጸዋል።
በዓሉ የመተዛዘን፣ የመረዳዳት እና የአብሮነት ዕሴት የሚገለጽበት መሆኑን የገለጹት አቶ ፀጋዬ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በረመዳን ወር ያከናወናቸውን መልካም ተግባራት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉም ገልጸዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና ልማትን ለማረጋገጥ በሚከናወኑ ተግባራት እያበረከቱ ያለውን አስተዋፅኦ ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ይኖርበታል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያን ከፍታን ማፅናት የሚያስችሉ ተምሳሌቶችን በመውሰድ ውስጣዊ አንድነትን ከሚሸረሽሩ ጉዳዮች መራቅ ያስፈልጋል ያሉት አቶ ፀጋዬ በኀብረ ብሔራዊ አንድነት የኢትዮጵያን ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ የሰላም፣የጤና፣የአንድነት እና የመተሳሰብ በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዒድ ሙባረክ!
መልካም በዓል!
አቶ ፀጋዬ ማሞ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ

More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ