የክልሉ የልማት ፖሊሲና ዕቅድ ትክክለኛ፣ ህጋዊና ሙሉ የሆነ መረጃ ላይ በመመስረት ምጣኔ ሀብትና ማህበራዊ ዕድገት እንዲረጋገጥ መስራት እንደሚጠበቅ ተገለፀ

የክልሉ የልማት ፖሊሲና ዕቅድ ትክክለኛ፣ ህጋዊና ሙሉ የሆነ መረጃ ላይ በመመስረት ምጣኔ ሀብትና ማህበራዊ ዕድገት እንዲረጋገጥ መስራት እንደሚጠበቅ ተገለፀ

ሀዋሳ፡ ሚያዝያ 01/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ በመረጃ አያያዝ አደረጃጀትና ጂ አይ ኤስ ሶፍት ዌር አጠቃቀም ዙሪያ በክልሉ በሚገኙ ዞኖች የተወጣጡ ለፕላንና መረጃ መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና በአርባ ምንጭ እየሰጠ ይገኛል።

ሥልጠናው በዋናነት በሶሾ ኢኮኖሚክ ፕላንግ በስነ ህዝብ እና በጂ አይ ኤስ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል።

የክልሉ የልማት ፖሊሲና ዕቅድ ትክክለኛ፣ ህጋዊና ሙሉ በሆነ መረጃ ላይ በመመስረት የክልሉን ምጣኔ ሀብታዊና ማህበራዊ ዕድገት እንዲረጋገጥ በማድረግ የመረጃ ተዓማኒነትና ጥራት ትልቅ ፋይዳ እንዳለ ይታመናል።

በስልጠናው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ የልማት መረጃና የሥነ ህዝብ ዘርፍ ኃላፍና የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ቱርቃቶ ቱርቶ ክልሉ በርካታ ብዝሃነትን የያዘ በመሆኑ መተማመንና አጠቃላይ ሥራዎችን በግልፀኝነት ማከናወን ያሻል ብለዋል።

አክለውም እያንዳንዱ መረጃ በአግባቡ በመሰብሰብና በጥራት ተንትኖ ህጋዊ በሆነ መንገድ ማቅረብ እንደሚገባ ተናግረው ሥልጠናው ለዚህ አቅም እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል።

የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት በሚያስረጋግጥ መልኩ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው በሥልጠና በሚያገኙት ግንዛቤ በመታገዝ ሥራዎችን በጥራት ለመሥራት ዝግጁ መሆን እንደሚገባቸውም አሳስበዋል።

ስልጠናው የመረጃ ሥርዓት የበለጠ ለማጠናከር ታልሞ እየተካሄደ መሆኑን የሚናገሩት የቢሮው ምክትል ኃላፊና በቢሮው የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊስ ጥናት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አርኮ ደምሴ ይህን የአቅም ግንባታን በመጠቀም በዘርፋ በአጽኖት እንዲሰሩም መክረዋል።

ተቋሙን የሚመለከቱ አዋጆችና ደንቦች ቀርበው ከሠልጣኞም አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል።

ዘጋቢ፡ አበበ ዳባ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን