እንኳን ለ1ሺህ 145ኛው አመት የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

እንኳን ለ1ሺህ 145ኛው አመት የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰመስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለ1ሺህ 145ኛው አመት የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመልዕክ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

“የረመዳን ወር በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ እጅግ የተከበረ አላህ እጅግ ውድ ስጦታዎቹን የሰጠበት፣ የእምነታቸው መመሪያ የሆነው ቁርአን ወደ ምድር የወረደበት፣ የጀነት በሮች የተከፈቱበት፣ አማኙ ከፈጣሪ ምንዳዎችን የሚያገኝበት የተቀደሰ ወር እንደሆነ ይታመናል።

ይህንን ወር በተለየ ዝግጅት ምዕመኑ ራሱን በፅድቅ በማትጋትና እና በማንፃት የተቀበለዉ ለሀገር ሠላም ለወገን ደህንነት የሚጸለይበት ነዉ።

በበዓሉ ቀንም ሕዝበ ሙስሊሙ እርስ በእርሱ እየተጠያየቀ፣ አብሮነቱንና አንድነቱን የሚያሳይበት፣ ያለው ከሌለው የሚረዳዳበት፣ ያገኘው ካላገኘው ምግብና ፍቅርን ተጋርቶ የሚያሳልፍበት ከእሴቱ ትሩፋቱ የሌላ እምነት ተከታዮችም የሚቋደሱበት ዕለት ነው።

ሀገራችንም ይሁን ክልላችን ብዝሃ ሃይማኖት ያላቸው ህዝቦች የሚኖሩባት ሲሆን የሁሉም ሀይማኖት አስተምሮ ትኩረት አብሮነት መቻቻል መረዳዳት መጠያየቅ መከባበር ነው።

ይህንን የሃይማኖቶች ሁሉ አስኳል ሃሳብ የሆነውን የአብሮነት የመረዳዳት የመከባበርና የመደጋገፍ ትዕዛዝና ልማድ እንደወትሮ ሁሉ ህዝበ ሙስሊሙ በዚሁ በዓልም እንደሚያስቀጥለው እምነቴ የፀና ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ህዝበ ሙስሊሙ ከሌሎች ወንድምና አህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ለሀገር ብልጽግና፣ ሠላምና ለተሻለ ነገ እያበረከተ ያለዉን አስተዋጽኦ እጠናክሮ እንዲቀጥል እጠይቃለሁኝ።

በድጋሚእንኳን ለ1ሺህ 145ኛው አመት የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!”

ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ