የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ የሁሉንም የጋራ ጥረት የሚሻ መሆኑ ተገለፀ

የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ የሁሉንም የጋራ ጥረት የሚሻ መሆኑ ተገለፀ

ሀዋሳ፡ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “በአመለካከትና በተግባር የተግባባ የብልጽግና አመራር መገንባት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ዞናዊ የአመራር የውይይት መድረክ በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የውይይት መድረኩ ከዚህ ቀደም በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች፣ ከተማ አስተዳደሮችና በዞን ማዕከል አመራሮች የተካሄደ ሲሆን አጠቃላይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የዞኑ ተወላጅ አመራሮችን ያጠቃለለ ነው።

በመድረኩም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤልን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።

ዘጋቢ: አማኑኤል አጤቦ – ከሆሳዕና ጣቢያችን