በረመዳን ጾም ወቅት የታየው የመረዳዳትና የመደጋገፍ መልካም ተሞክሮ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አስታወቀ
ለ1 ሺህ 4 መቶ 45ኛ ጊዜ ለሚከበረዉን የኢድአልፈጥር በዓል መሰረት የሆነዉ የረመዳን ወር ጾምና ጸሎት በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች በሰላማዊ ሁኔታ እተከናወነ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡
ከአምስቱ የእስልምና እምነት መሠረቶች ዉስጥ አንዱ እንደሆነ የሚታመነዉ የረመዳን ወር በመላዉ አለም በሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበር በዓል መሆኑን የገለጹት በቦንጋ ከተማ ከሚገኙት የእምነቱ ተከታዮች መካከል አንዳንዶቹ የዘንድሮው የረመዳን ወር ጾም በሰላማዊ ሁኔታ እየተከወነ ነው ብለዋል፡፡
ረመዳን ከእስላማዊ የእምነት ግዴታዎች አንጻር መደጋገፍና መተባበርን አጥብቆ ያስተምራል ያሉት የደቡብ ምዕራብ እትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እስልምና ጉዳይ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሸረፈዲን ኑሩ ይህን የፈጣሪ ትዕዛዝ ባለማጓደል ያለንን በማካፈል የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል በማለት ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡
ከዚህ በፊት በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ እንደተለመደው በዘንድሮዉ የረመዳን ወር ጾም ወቅት ከሁሉ ከእምነቱ ተከታዮች በተሰበሰበ ዘካ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን የተናገሩት አቶ አብዱርዛቅ አብደላ ይህም ትልቅ ሰብዓዊ ተግባር ነው ብለዋል፡፡
በረመዳን ወር ጾም ዉስጥ ዱኣ፣ ዘካና ሰደቃ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውና በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በክብር የሚደረግ ተግባር ነው ያሉት አቶ ሸረፈድን ለሀገርና ህዝብ ሰላም መጸለይ ደግሞ በእስላምና እምነት ተከታዮች ሁሌም የሚዘወተር ነው ብለዋል፡፡
መጠያየቅ፣ መደጋገፍና መዋደድ በቅርብ ካለዉ ጎረቤት ጀምሮ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተሰጠ ሀላፊነት ነው ያሉት ወ/ሮ ዘምዘም ኑሩ ይህንን ሃይማኖታዊ ግዴታ ሁሉም በትጋትና በእምነት ሊፈጽም ይገባል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አሳምነው አትሳው – ከቦንጋ ጣቢያችን
More Stories
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት ኘሮጀክት አስተባባሪዎች እና የግብርና ሚንስቴር ብሔራዊ ኘሮጀክት ልዑክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የድርቅ መቋቋሚያና ዘላቂ የአርብቶ አደር ኑሮ ማሻሻያ ኘሮጀክት የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
የከተማዋን መሠረተ ልማት ለማስፋፋት በሚደረገው ሂደት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የቀለጣ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠሪያ ጊዜን በማፋጠን ኢትዮጵያን የመጪው ዘመን መሪ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለጸ