አንድ መፅሐፍ ለአንድ ተማሪ በሚል መሪ ሀሳብ ለአንድ ወር የሚቆይ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እየተካሄደ ነው

በክልሉ ርእሰ መስተዳድር በአቶ ጥላሁን ከበደ ሀሳብ አመንጪነት ነዉ የመፅሀፍ የማሰባሰብና የመለገስ መርሃ ግብሩ በመካሄድ ላይ ያለው ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፅ/ቤትና የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሚያስተባብሩት መርሃ ግብር ላይ የክልሉን ርእሰ መስተዳድር ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው ።

በመርሃ ግብሩ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ለአንድ ወር በሚቆየዉ መፅሐፍ የማሰባሰብና የመለገስ ዘመቻ ላይ ሁሉም በንቃት በመሳተፍ በክልሉ በየደረጃዉ በሚገኙ  ትምህርት ቤቶች ላጋጠመው የመፅሀፍ እጥረት በማቃለል አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል ።

መድረኩ ለትምህርት ስብራት ሁሉም መፍትሄ ከመፈለግና የራሱን አሻራ ከማሳረፍ ባለፈ በክልሉ የእስካሁኑ ጉዞና በቀጣይ እቅድ ላይ የሚመከርበት እንደሆነም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል ።

ክልሉን ህዝቡን በማሳተፍ የብልፅግና ተምሳሌት እንዲሆን በእቅድ በሰራነው ስራ የተሻለ ተግባር መከናወን መቻሉን ስለመገምገሙ አስረድተዋል ።

በእቅድ በተያዙ ቀሪ ተግባራት ላይ የተሻለ ስራ ለመስራት በእቅድ በማስደገፍ በልዩ ርብርብ ይሰራል ብለዋል ።

በክልሉ ምክር ቤት በተነሱና አንገብጋቢ የህዝብ ጥያቄን በተደራጀ መልኩ ለመምራት የ100 ቀናት እቅድ መዘጋጀቱንና ይህንንም በመድረኩ በጥልቀት በመምከር ወደ ስራ መገባት አስፈላጊ በመሆኑም መድረኩ አፅንኦት ሰጥቶ መምከር አለበት ብለዋል ።

ዘጋቢ፡ ጸጋአብ ዮሃንስ