”ትጉህና አገልጋይ ሲቪል ሰርቫንት ለከተሞች ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የፈጻሚ የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው

”ትጉህና አገልጋይ ሲቪል ሰርቫንት ለከተሞች ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የፈጻሚ የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማና ኢንደስትሪ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል በክልሉ በ 7ቱም ማዕከላትና በጥቅሉ በ 183 ከተሞች የፈጻሚዎች መድረክ እየተካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህ ውይይት ፈፃሚው ሰራተኛ እንደ ግል እና ተቋማዊ ጉድለቶችን በዝርዝር ነቅሶ በመለየት በመፍትሔዎቹ ላይ ተግባቦት ላይ እንዲደርስ ይደረጋል ነው ያሉት ።

የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ችግሮች ደረጃቸው ቢለያይም ችግሮቹ በፈጻሚውም በተገልጋዩ ህብረተሰብም የሚታይ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።

በተገልጋይ በኩል የሚሰተዋሉ የግንዛቤና ሌሎች ጉድለቶችን ለመቀነስና የተገልጋዩን ተሳትፎ ለማሳደግ በመጋቢት 26/2016 ዓ.ም በክልሉ ባሉ ሁሉም  ከተሞች ” ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለህዝባችን “በሚል መሪ ቃል  ከከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ይካሄዳል ብለዋል።

በመድረኩ የአገልግሎት አሠጣጥና መልካም አስተዳደር ችግሮችን የመለየትና ስለመፍትሄዎቹ ተግባቦት ለመድረስ ያለመ ስለመሆኑም የቢሮ ሀላፊው ጠቁመዋል።

በውይይት መድረኮቹ በፈፃሚው አካል በኩል በተለዩ ችግሮችና በተገልጋዩ በኩል በሚስተዋሉ ችግሮች ላይ በመግባባት በሚቀጥሉ አጭር፣መካለኛና ረጅም ጊዜያት ችግሮቹ በሚፈቱበት መንገዶች ላይ የሁለቱም አካላት ሚና ተግባቦት የሚፈጠር ይሆናል ሲሉ አቶ ስንታየሁ ተናግረዋል ።

ባለፉት 9ወራት ዕቅድ አፈፃፀምና 2ኛ ዙር 100 ቀናት አፈፃፀም ላይ ያተኮረ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን በዚህ ወር በትኩረት እየተፈፀመ ያለ ተግባር  ነውም ብለዋል።

የከተማ ነዋሪዎች ህይወት ሁለንተናዊ ለወጦች ለማምጣት የተጀመሩ ተግባራት ላይ በሙሉ ትኩረትና አቅም መረባረብ ይገባል ሲሉ አስረድተዋል ።

ዘጋቢ ፡ አብደላ በድሩ