በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተሰናዳው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 17/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የተሰናዳው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪ ኤግዚቢሽን በክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተጎብኝቷል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የኢንቨስትመንት፣ ኢንዱስትሪና የግብርና ልማት ውጤቶች በኤግዚቢሽኑ ለዕይታ የቀረቡ ሲሆን፥ የማኑፋክቸሪንግ ልማት ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ስኬት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ለማስቻል የግሉ ዘርፍ እንዲጎለብትና የዕድገት አማራጮችን ለማስፋት አስተዋጽኦ እንዳለው ተመልክቷል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤልን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎች በጉብኝቱ ላይ እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ

More Stories
የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር የምርጥ ዘር ብዜት ስራን በራስ አቅም ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምርጥ ዘር ድርጅት አስታወቀ
በበልግ አዝመራ ከሚከናወኑ የግብርና ስራዎች ከ70 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዷል – አቶ ማስረሻ በላቸው
የመንግሥትን የልማት ክፍተቶችን ለመሙላት የሚሰሩ የማህበረሰብ ልማት ድርጅቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በተሻለ ለማረጋገጥ በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል – አምባሳደር ፍጹም አረጋ