የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የእንሰት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሁሉም ሊረባረቡ ይገባል
ሀዋሳ፡ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጌዴኦ ዞን የእንሰት ተሃድሶ በሚል መሪ ቃል የእንሰት ልማት ንቅናቄ መድረክ በዲላ ከተማ ተካሂዷል።
የጌዴኦ ዞን የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ታጠቅ ዶሪ እንሰት ለዞኑ አርሶአደሮች የገቢ ማስገኛ ፣ መተዳደሪያ፣ የምግብ ዋስትናና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ነው ብለዋል፡፡
የዘርፉን ምርት ለማሳደግም የምርምር ሥራዎችን በመሥራት ለውጦች መታየት መተጀመራቸውን የተናገሩት ኃላፊው ለውጡን ማስቀጠል እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ በዘመቻና በተሀድሶ የእንስት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስረድተዋል ።
በ2014 ዓ.ም የተጀመረው የምዕራፍ -1 የንቅናቄ ሥራ እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ 68 ሚሊዮን ችግኞች እንደተተከሉ ልጸዋል፡፡
በ2016 ዓ.ም ከ40 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል መታቀዱን አብራርተዋል ፡፡
የግል ድርጅቶች በመረዳዳትና በመደጋገፍ የእንስት ተከላ ሥራ ለማስፋፋት በቅንጅት በመሥራት የምግብ ዋስትናን ለማረጋግጥ የየበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ እንሰት ከምግብነትም አልፎ ለማህበራዊ፣ ለኢኮኖሚና ለኢንዱስትሪው የሚያገለግል ዋና የግብርና ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እንሰት ለምግብነት ለቤት መስርያነት፣ ለመድኃኒትነትና ለኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃነት ከማገልገልም ባለፈ ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ውሃን ለረጅም ጊዜ ይዞ በማቆየት ድርቅን የሚቋቋም ስብል ነው ብለዋል፡፡
በእንስት ልማት ሥራ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት የምስጋናና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
በዞኑ ከመጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 02 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ የእንሰት ሳምንት ታውጆ በንቅናቄ የተከላ ሥራ እንደሚከናወን ተገልጿል፡፡
ዘገቢ:- ፅጌ ደምሴ- ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ የሚባክነውን የህዝብና የመንግሥት ሀብት ማዳን መቻሉ ተገለጸ
ቅንጅታዊ አሠራርን በማስፈን ጥምር ደን መጠበቅ፣ ማስፋትና መጠቀም እንደሚገባ ተጠቆመ
የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን በማዘመን የዘርፉን ውጤታማነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለፀ