በቀጣዩ ዓመት ከ3 ቢሊዮን ዩሮ በላይ ገንዘብ ለክለቦች እንደሚከፍል የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታወቀ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር በሚቀጥለው ዓመት በስሩ በሚካሄዱ ውድድሮች ተሳተፊ ለሆኑ ክለቦች አጠቃላይ 3 ነጥብ 317 ቢሊዮን ዩሮ እንደሚከፍል አስታውቋል።
ከዚህ ውስጥ ማህበሩ 2 ቢሊየን 467 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 74 በመቶ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ እና ለአውሮፓ ሱፐር ካፕ ውድድር መመደቡን ገልጿል።
እንዲሁም 565 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 17 በመቶ ለዩሮፓ ሊግ ወጪ እንደሚያደርግ ያሳወቀ ሲሆን፥ 285 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 8 ነጥብ 6 በመቶ ድርሻ ደግሞ ለኮንፍረንስ ሊጉ እከፍላለሁ ብሏል።
በአከፋፈል ሂደቱ መሰረት በቀጣዩ የውድድር ዓመት የተሳታፊ ክለቦች ቁጥር ወደ 36 ከፍ በሚለው የአውሮፓ ሻምፒዮንስሊግ የሚሳተፉ ክለቦች እያንዳንዳቸው 18 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ክፍያውን የሚያገኙ ይሆናል።
ከምድብ ማጣሪያ በመቀጠል በሚካሔዱ እስከ ፍፃሜ ድረስ ባሉ የጥሎ ማለፍ ጨዎታዎች በየዙሩ ተጨማሪ 4 ነጥብ 29 ሚሊዮን እንደሚከፍልም ከማህበሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።
የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የዋንጫ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ ደግሞ 86 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ክፍያ ከአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እንደሚፈፀምለት ይፋ ተደርጓል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
ሀዋሳ ከተማ መቀሌ 70 እንደርታን አሸነፈ
ኦክስሌድ ቻምበርሌን በአርሰናል ልምምድ መስራት ጀመረ
ቱርክ 149 የእግር ኳስ ዳኞችን አገደች