ምሽቱን በተካሄዱ ሁለት የፍፃሜ ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸነፉ
በ13ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ሩጫ ውድድር የወርቅና የብር እንዲሁም በ800 ሜትር ሴቶች የወርቅ ሜዳልያን አሸንፋለች።
በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ፍፃሜ አትሌት ንብረት መላክ 29:45.37 በሆነ ሰዓት ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅ ገመቹ ዲዳ 29:45.68 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል።
አትሌት ፅጌ ዱጉማ በ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ 1:57.73 በሆነ ሰዓት 1ኛ ሆና በመግባት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳልያ አስገኝታለች።
በጋና እየተካሄደ በሚገኘው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያ እስካሁን 4 ወርቅ፥ 3 ብር እና 1 የነሃስ ሜዳልያን መያዝ ችላለች።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
ማንቸስተር ሲቲ በአዲሱ የውድድር ዓመት 2ኛ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገደ
ማንቸስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል
ጄሚ ቫርዲ ወደ ጣሊያን ሴሪኣ ሊያቀና ነው