“ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ ኮንፈረንስ መካሔድ ጀመረ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ቃል በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ ኮንፈረንስ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ እንዳሻው ጣሰው እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ከክልሉ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ የፓርቲው አባላት በኮንፍረንሱ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የኮንፍራንሱ አላማም በዋናነት ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል ከልማት አንፃር ምን ተሰራ ምንስ ይቀራል የሚለውን በስፍት ለመመልከት ያግዛል ተብሏል።
ኮንፍረንሱ ከቀበሌ ጀምሮ በየመዋቅሩ ሲካሄድ የመጣና ይህም ክልላዊ ማጠቃለያ ነው።
በኮንፍረንሱም ከ1ሺ በላይ የክልሉ የፓርቲው አባላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡ ቃልአብ ጸጋዬ

More Stories
ብሔራዊ ምክክር ሀገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባሻገር ችግሮችን በውይይትና በሀሳብ የበላይነት ለመፍታት መሠረት እንደሚጥል ተገለጸ
የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 ጠቋሚ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ አርሶ አደሮች የመኸር እርሻ የማሳ ዝግጅት ቢያደርጉም በቂ ግብዓት አለማግኘታቸውን ገለጹ