የደሬቴድ ዲጂታል ሚዲያ የመጋቢት 12/2016 ዓ.ም የዕለቱ ዋና ዋና ዜናዎች፡-
👉የፌደራል ድጋፍ ሰጪ እና ሱፐርቪዥን ልዑክ በሲዳማ ክልል እያደረገ ያለውን ድጋፍ በማጠናከር በዛሬው ዕለት በክልሉ ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አርቤጎና ወረዳ በመገኘት የቱሪዝም መዳረሻ የሆነውን የጋራምባ ተራራን ጎበኘ።
👉በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር በዶ/ር አለሙ ስሜ የተመራ የፌደራሉ ሱፐርቪዥን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን በሀምበርቾ ተራራ ላይ የተገነባውን የ777 ኢኮ ቱሪዝም ሥፍራን ጎበኘ::
👉የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንትና የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ሳልቫ ኬር ማያርዲት የሀገሪቱን ታላቁን ኒሻን ለኢፌዴሪ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አበረከቱ።
👉በአምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የሚመራው የፌደራሉ የሱፐርቪዥን ቡድን በምስራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ የተሻሻለና ለውጭ ገበያ የሚውል የአቮካዶ ዝርያ ተመለከተ።
👉የማህበራዊ ብልጽግና ጉዞን ለማሳለጥ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ያረጋገጠ ማህበረሰብ መፍጠር ቁልፍ ተግባር ነው ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለፁ፡፡
👉በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ያለመ የምክክር መድረክ ከባለሀብቶች ጋር በቡታጅራ ከተማ ተካሄደ።
👉በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በህብረተሰብ ተሳትፎ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመማሪያ መጽሀፍት ህትመት ስራ መከናወኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ ገለጹ፡፡
👉በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ2016 በጀት አመት 272 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን የክልሉ ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ