ቤን ኋይት በአርሰናል ለመቆየት ኮንትራቱን ለተጨማሪ ዓመታት አራዘመ
እንግሊዛዊው ተከላካይ ቤን ኋይት በአርሰናል ለተጨማሪ ዓመታት የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ተፈራርሟል።
ሁለገቡ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች በኤምሬት እኤአ እስከ 2028 ድረስ እና ለተጨማሪ ዓመት የሚያቀቆየውን ውል ነው የተፈራረመው።
በ2021 ከብራይተን አርሰናልን የተቀላቀለው ኋይት ለሰሜን ለንደኑ ክለብ እስካሁን 121 ጨዋታዎችን በሁሉም ውድድሮች ተሰልፎ አከናውኗል።
ዘጋቢ፤ ሙሉቀን ባሳ

More Stories
“ከማክስ ዶውማን ጋር መስራት ትልቅ ደስታ ነው” ሚኬል አርቴታ
ስፖርት ፍቅርን፣ ሰላምን እና አንድነትን ለማምጣት ወሳኝ ነው – የቡርጂ ዞን አስተዳደር
“እናቴ ሆይ ደውይልኝ!”