የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ያቀረባቸውን 5 አዋጆች ምክር ቤቱ አጸደቀ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ ያቀረባቸውን 5 አዋጆች ተቀብሎ አጽድቋል።
ረቂቅ አዋጆቹን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ጠንክር ጠንካ የ5ቱን አዋጆችና ዝርዝር ይዘት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ጠንክር ጠንካ፥ ለምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ፥ የረቂቅ አዋጆቹን አስፈላጊነት በዝርዝር አስረድተዋል።
ረቂቅ አዋጆቹ በቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት ተገቢው ውይይት እና ምክክር የተደረገባቸው ሲሆን፥ የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባትና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሁም ከክልሉ ህገ መንግስት ጋር እንዲጣጣሙ ተደርገው መዘጋጀታቸውን አቶ ጠንክር ለም/ቤቱ ገልፀዋል።
በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ የቀረበለትን 5 ልዩ ልዩ የግብርናና ገጠር ልማት ቋሚ ኮሚቴ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።
1, የደቡብ ኢትጵያ ክልላዊ መንግስት የኮንሶ ባህላዊ መልክአ-ምድር ቅርሶችን ለመጠበቅ የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
2, የደቡብ ኢትጵያ ክልላዊ መንግስት የጌዴኦ ባህላዊ መልክአ-ምድር ቅርሶችን ለመጠበቅ የወጣ ረቂቅ አዋጅ፣
3, የደቡብ ኢትጵያ ክልላዊ መንግስት የማዕድን ስራዎችን ለማስተዳደር የወጣ አዋጅ፣
4, የደቡብ ኢትጵያ ክልላዊ መንግስት የዱር ህይወት ጥበቃ፣ ልማትና አጠቃቀም አዋጅ፣
5, የደቡብ ኢትጵያ ክልላዊ መንግስት የውሃና ፍሳሽ አገለግሎት ድርጅት አዋጅ
በቀሩቡት አዋጆች ዙሪያ የምክር ቤት አባላት በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ተጨማሪ ሃሳብና አስተያየት የሰጡበት ሲሆን፥ አዋጆቹ ተጨማሪ ግብዓት ታክሎባቸው ም/ቤቱ በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ አጽድቋል።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ

More Stories
በተቀሩት አጭር ቀናት ህብረተሠቡ የመራጭነት ካርዱን በመውሰድ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳና አካባቢው የፌደራልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ አቀረቡ
ማህበራዊ ሚዲያ ጊዜና ቦታ ሳይገድበው መረጃን በፍጥነት ተደራሽ ስለሚያደርግ ተጠቃሚዎች ትክክለኛ እና ተአማኒነት ያለውን መረጃ ማሰራጨት ይጠበቅባቸዋል – ዶ/ር በኃይሉ ገ/ማሪያም
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 25 ሺህ 338 ሊትር ቤንዝልና 62 ሺ 686 ሊትር ናፍጣ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ