የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የከተሞች ፕላንና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለትን አዋጆች መርምሮ አጸደቀ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በከሰዓት ውሎ የከተሞች ፕላንና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ያቀረባቸውን 6 አዋጆች እንዲያጸድቅለት ለምክር ቤቱ አቅርቧል።
ረቂቅ አዋጆቹን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የከተሞች ፕላንና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እንቁ ዮሐንስ የ6ቱን አዋጆችና ዝርዝር ይዘት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ እንቁ ዮሐንስ፥ ለምክር ቤቱ በሰጡት ማብራሪያ፥ ረቂቅ አዋጆቹ አስፈላጊ የሆኑበትን ምክንያት አስረድተዋል።
ረቂቅ አዋጆቹ በቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት ተገቢው ውይይት እና ምክክር የተደረገባቸው ሲሆን የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባትና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ እንዲሁም ከክልሉ ህገ መንግስት ጋር እንዲጣጣሙ ተደርገው መዘጋጀታቸውን አቶ እንቁ ለም/ቤቱ ገልፀዋል።
በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ የቀረበለትን 6 ልዩ ልዩ የከተሞች ፕላንና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።
1, የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ፣
2, የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የቆሻሻ አያያዝ፣ አወጋገድ እና ቁጥጥር አዋጅ፣
3, የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የስታትስቲክስ ስርዓትን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ፣
4, የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የፕሮጀክቶች አስተዳደር ለመደንገግ የወጣ አዋጅ፣
5, የደቡብ ኢትጵያ ክልላዊ መንግስት የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ፣
6, የደቡብ ኢትጵያ ክልላዊ መንግስት የጫት ኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ፣
በቀሩቡት አዋጆች ዙሪያ የምክር ቤት አባላት በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ተጨማሪ ሃሳብና አስተያየት የሰጡበት ሲሆን፥ አዋጆቹ ተጨማሪ ግብዓት ታክሎባቸው ም/ቤቱ በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ አጽድቋል።
ዘጋቢ፡ ዘላለም ተስፋዬ
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ