ማውሪዚዮ ሳሪ ከላዚዮ አሰልጣኝነት በገዛ ፈቃዳቸው ተሰናበቱ
ጣሊያናዊው አሰልጣኝ ማውሪዚዮ ሳሪ ከላዚዮ አሰልጣኝነት በገዛ ፈቃዳቸው ራሳቸውን አንስተዋል።
የ65 ዓመቱ አሰልጣኝ እኤአ በ2021 ላዚዮን በዋና አሰልጣኝነት የተረከቡ ሲሆን በያዝነው የውድድር ዓመት የጣሊያን ርዕሰ መዲናውን ክለብ ውጤታማ ማድረግ ባለመቻላቸው ሃላፊነቱን ለቀዋል።
ላዚዮ በሴሪአው ከ28 ጨዋታዎች በ12ቱ ተሸንፎ 40 ነጥቦችን በመያዝ 9ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ማውሪዚዮ ሳሪ ላዚዮን ከማሰልጠናቸው በተጨማሪ ኢምፖሊን፥ናፖሊን፥ቼልሲን እንዲሁም ዩቬንቱስን በአሰልጣኝነት መምራታቸው ይታወሳል።
ዘጋቢ፡ ሙሉቀን ባሳ
More Stories
የ2017 የጋሞ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ውድድር በወንዶች እግር ኳስ ውድድር በዳራማሎ ወረዳ አሸናፊነት ተጠናቀቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጅቡቲ አቻውን 6ለ1 አሸነፈ
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ የምስክር ወረቀት ተሰጠው