የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤዉን ማካሄድ ጀመረ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምዕራብ ኦሞ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 11ኛ አመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤዉን በዞኑ ማዕከል ጀሙ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ቢልልኝ ወልደሰንበት፤ ምክር ቤቶች የዴሞክራሲ ባህል እንዲሰፍን በማድረግ የሕዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ በኩል ሚናቸዉ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።
በዚህም የዞኑ ምክር ቤት በአስፈጻሚ አካላት የሚከናወኑ ተግባራትን ከመደገፍና ከመቆጣጠር ጀምሮ የሕዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ማከናወናቸውን ተናግረዋል።
የሕዝቡን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የቀበሌ ምክር ቤቶችን አቅም በመገንባት በኩል ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።
በመድረኩ የዞኑ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ቀርቦ የፀደቀ ሲሆን የአስተዳደር ምክር ቤት የ2016 ዓ.ም የግማሽ አመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።
ጉባኤዉ የሁለት ቀን ቆይታ የሚኖረው ሲሆን በቀረበዉ ሪፖርት ላይ ዉይይት በማድረግ የተለያዩ ሹመቶች ቀርበዉ እንደሚፀድቁ ከወጣዉ መረሃ ግብር መረዳት ተችሏል።
ዘጋቢ፡ ዮሐንስ አሰፋ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ