ስፖርታዊ ውድድሮች ለማህበራዊ ወዳጅነትና አብሮነት የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ
ሀዋሳ፡ መጋቢት 03/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ስፖርታዊ ውድድሮች ከመዝናኛነት ባለፈ ለማህበራዊ ወዳጅነትና አብሮነት የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት አሪ ዞን የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች በጂንካ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ስፖርት ወንድማማችነትን በማጠናከር ስላምን ለማስፈን ሚናዉ የጎላ ነው ያሉት የአሪ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የውድድርና ተሳትፎ ቡድን መሪ እና የውድድሩ አዘጋጅና ስነ-ስረዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አየናቸዉ ጥላሁን በበኩላቸው በዞኑ ውስጥ ያሉ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ያላቸዉን የወንድማማችነትና እህትማማችነት ስሜት በማጠናከር በዞኑ እየተቀዛቀዘዘ የመጣዉን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማስቀጠል ታቅዶ እየተካሄደ ያለ ስፖርታዊ ውድድር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
አክለዉም ወጣቱ በተለያዩ ሱሶች ተጠምዶ ጊዜዉን አልባሌ ቦታ እንዳያሳልፍ በስፖርታዊ ውድድር ውስጥ በማሳተፍ አምራች ዜጋን ለማፍራት እየተሰራ ነውም ብለዋል፡፡
የጂንካ እና ገሊላ ከተማዎች እግር ኳስ ቡድን መሪ አቶ ንጉሴ ታዬ እና መኮንን እውነቱ በጋራ እንደገለፁት፤ መሠል ስፖርታዊ ውድድሮች ከየአከባቢ የሚመጡ ሰዎችን በአንድ ሜዳ በማገናኘት የተለያዩ ተሞክሮችን እርስ በእርስ እንዲለዋወጡና ለሰላምና ለልማት አብረው እንዲሰለፉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው፡፡
የዎባ አሪ ወረዳ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን አምበል ምናሴ ሳሙኤል እና የባካዳዉላ አሪ ወረዳ የሴቶች እግር ኳስ ተጫዋች ጥሩወርቅ ኢሳያስ፤ የስፖርት ዋና አላማው አንድነትና ፍቅር በመሆኑ እየተካሄደ ያለዉ ስፖርታዊ ውድድር በዞኑ በመልካዓም ምድርና በመዋቅር የተራራቁ ስዎችን የሚያቀራርብ በመሆኑ በውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ እየተሳተፉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ስፖርት ለአብሮነት ለሰላምና ለእርስ በእርስ ግንኙነት ካለዉ ከፍተኛ ሚና አንፃር ውድድሩ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ በሰላምና ፀጥታ ማስከበሩ ረገድ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የአሪ ዞን ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል ድቪዥን የኦፕሬሽን አመራር ምክትል ኢንስፔክተር ታሪኩ ጀኣ ተናግረዋል፡፡
ውድድሩ በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ የስፖርቱ ቤተሰብ የድርሻቸዉን መወጣት እንደሚገባቸዉም ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ቼልሲ ሌስተርን አሸነፈ
ሮድሪጎ ቤንታንኩር ከእግር ኳስ ጨዋታዎች ታገደ
በቀቤና ልዩ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ 5ተኛ አመት ምስረታን ምክንያት በማድረግ ማህበረሰብ አቀፍ የማስ ስፖርት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል