ከ100 በላይ  ግብር ከፋዮች ላይ  የእርምት እርምጃ  መውሰዱን የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ

ከ100 በላይ  ግብር ከፋዮች ላይ  የእርምት እርምጃ  መውሰዱን የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ

ሀዋሳ፡ መጋቢት 04/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በተደረገው የህግ  ማስከበር  ሥራ   ከ100  በላይ  ግብር ከፋዮች ላይ  የእርምት እርምጃ መውሰዱን የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ አስታወቋል። 

የጌዴኦ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌቱ  ታምሩ እንደተናገሩት መምሪያው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መጋቢት  03 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው ኦፕሬሽን 6 ግብር  ከፋዮች  ግብር በማጭበርበርና ደረሰኝ ባለመስጠት  በህግ ቁጥጥር ሥር ውለው የምርመራ ሥራ እየተከውነ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተደረገው ድንገተኛ የታክስ ኦፕሬሽን  በ107  ግብር  ከፋዮች ላይ  አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎችን መውሰዳቸውን   ጠቁመው ተግባሩ  በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

የግብር ማጭበርበር ባደረጉ ግብር ከፋዮች ላይ በተደረገው የህግ  ማስከበር ተግባር 1 ሚሊዮን 830 ሺህ 60 ብር   ወደ  መንግስት ካዝና ገቢ ተደርጎል ነው ያሉት፡፡

የክትትልና ህግን የማስከበሩ ሥራ በዞኑ  ዲላ፣ ይርጋጨፌ እና ገደብ ከተሞች ላይ መካሄዱን ገልጸው  ሕብረተስቡ  ግብር   የሚሰውሩ  አካላት ላይ አስፈላጊውን ጥቆማ በመሰጠት የተጀመረውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን በቅንጅት መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

ዘጋቢ:-  ፅጌ ደምሴ ከይርጋጨፌ ጣቢያች።