የኬሌ ከተማ አስተዳደር ጊዜያዊ አማካሪ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 5ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አካሄደ
ጉባኤውን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የኬሌ ከተማ አስተዳደር ዋና አፈ-ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ ሀና ኃይሌ ለከተማው ልማት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ብለዋል።
ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለዜጎች ኑሮ የሚመች ከተማ ለመፍጠር ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገት ማስመዝገብ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ መልካሙ አስፋው በቅርቡ ወደ ከተማ የታቀፉ ቀበሌያት አደረጃጀት ሞሽን ሰነድ አቅርበው አስቸኳይ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የኬሌ ከተማ ከንቲባ አቶ ዮሐንስ ኃይሉ በበኩላቸው በከተማው ሥር ያሉ የቀበሌ ወሰን መካለል፣ የሰው ቁጥር መረጃና ስያሜ በታችኛው የቀበሌ ምክር ቤት እንደሚጸድቅ አስረድተዋል።
ከጉባኤው ተሳታፊዎች መካከል የኮሬ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አስታረቀኝ አንደባ የምክር ቤቱ አባል አቶ ፍጹም አራጋው እና ሌሎችም በሰጡት አስተያየት የቀበሌ አደረጃጀት የከተማውን ህብረተሰብ ጥያቄ የሚመልስ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡
በከተማ አስተዳደሩ ሥር ባሉ ሴክተሮች ላይ ሹመት በማጽደቅ ጉባኤው ተጠናቋል።
ዘጋቢ: ምርጫ መላኩ- ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ብሔራዊ ምክክር ሀገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባሻገር ችግሮችን በውይይትና በሀሳብ የበላይነት ለመፍታት መሠረት እንደሚጥል ተገለጸ
የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 ጠቋሚ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ አርሶ አደሮች የመኸር እርሻ የማሳ ዝግጅት ቢያደርጉም በቂ ግብዓት አለማግኘታቸውን ገለጹ