የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያየ ይገኛል
የኢንቨስትመንት መሬት የተላለፈበት መንገድና በሂደቱ የታዩ ችግሮች ቀርበው ውይይት ተካሂዷል።
በክልሉ መስፈርት ያሟሉ 77 ፕሮጀክቶች መሬት እንዲሰጣቸው የሚል የውሳኔ ሃሳብ ኮሚቴው አቅርቧል።
ሌሎች አንዳንድ መስፈርቶችን ያላሟሉ 35 ኘሮጀክቶች ሟሟላት ያለባቸውን በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ሲያሟሉ መሬት እንዲሰጣቸው የሚል የውሳኔ ሃሳብ ቀርቧል።
29 ኘሮጀክቶች ውድቅ ተደርገዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ የተጭበረበረ የባንክ ስቴትመንት ማቅረብ፣ የተዛባ መረጃ ማቅረብ፣ በዞን አካባቢ የተሰጠው የኢንቨስትመንት ፈቃድና ለክልሉ የሚላከው ሌላ ሆኖ መገኘት ጉዳዩን በተከታተለው ኮሚቴ የታዩ ችግሮች በሚል ተዘርዝሯል።
ኮሚቴው ግልፅ አሰራር፣ የህግ ማዕቀፍና ወጥ ስታንዳርድ መኖር አለበት የተባለ ሲሆን በመንግስትም ይሁን በባለሃብቱ በኩል ተጠያቂነትን መሠረት ያደረገ አካሄድ መከተል እንደሚገባ ኮሚቴው ጠቁሟል።
መስተዳድር ምክር ቤቱ በክልሉ የሰባት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ይመክራል።
የሰው ሃይል የመዋቅር ጥናት የደረሰበትን ደረጃ ይመለከታል፡፡ ልዩ ልዩ አዋጆችና ደንቦች ላይ ውይይት እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል።
ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ

More Stories
እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ሥራ ከዳር ለማድረስ በሚደረገው ርብርብ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሙዱላ ከተማ አስተዳደር ገለፀ
በትምህርት ሴክተር የመረጃ አያያዝ ውጤታማነት ዙሪያ በኩረት እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
ሁሉንም የመማሪያ መጻሕፍት ባለማግኘታቸው በትምህርታቸው ላይ ጫና እየፈጠረባቸው መሆኑን በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ የቆንጋና ቆቄ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተናገሩ