በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስርዓት የምግብና የሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራ አጋዥ የሆኑ ምክር ቤቶችን ማቋቋም ስለሚቻልበት ሁኔታ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንደሻው ጣሰው በተገኙበት በሚካሄደው በዚህ መድረክ በጤና ሚኒስቴር የስነ-ምግብ የስርዓተ ምግብ መሪ አስፈፃሚ ህይወት ዳርስኔ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በስርዓተ ምግብ አለመስተካከልና በመቀንጨር ችግር ምክንያት ኢትዮጵያ በዓመት 55.5 ቢሊየን ብር እንደምታጣ አስታውሰው በአመጋገብ ስርዓት ግድፈት የሚከሰቱ ችግሮችን ለማስወገድ የምግብ ስርዓትና ስርዓተ ምግብ ምክር ቤት ማቋቋም ማስፈለጉን ገልፀዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ አስራ አራት ወረዳዎች የሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራ ውስጥ ተገብቷል ብለዋል ሃላፊዋ።
የሰቆጣ ቃል ኪዳን እስከ ፈረንጆቹ አቆጣጠር 2030 ዕድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች በሆኑ ህፃናት የሚያጋጥም የተመጣጠነ የምግብ እጥረት እንዲቀረፍ የሚሰራ የስምምነት ማዕቀፍ ነው።
ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ

More Stories
በ6 ወራት ውስጥ ሊመዘበር የነበረ ከ156 ሚሊየን 560ሺህ ብር በላይ ማዳን መቻሉ ተገለጸ
የጉራጌ ክትፎ ባህልና እውቀትን በዩኒስኮ የሰው ልጆች ወካይ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ እየተሰራ እንደሚገኝ የኢፌዲሪ ቅርስ ባለስልጣን ገለፀ
በክልሉ ያሉ ብሔረሰቦችን ባህል ወደፊት በማውጣት የአካባቢውን ሰላምና ልማት ለማስቀጠል በትኩረት መስራት እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ተናገሩ