የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በስፋት እየታየ ያለውን የሥራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መሥራት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
የጌዴኦ ዞን የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕሪይዞች ልማት መምሪያ ከኦሞ ባንክ ዲላ ዲስትሪክት ጋር በመተባበር የሥራ ዕድል ፈጠራ ንቅናቄ መድረክ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አበባየሁ ኢሳያስ የኢኮኖሚ ችግርን ለመፍታትና የሥራ ዕድል በመፍጠር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም በቁጠባና ብድር አመላለስ ላይ የተጀመሩ የፖሊሲ ማስተካከያዎችን ተግባር ላይ በማዋል የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የማሳደግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ በኦሞ ባንክ የዲላ ዲስትሪክት ኃላፊ አቶ ጌታቸው በራሶ፣ የዞኑ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አበባየሁ ኢሳያስ እና ሌሌች የዞኑ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ፅጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
በእንስሳት እርባታ ከተሰማራን ወዲህ ኑሯችን ተሻሽሏል – የጋዘር ከተማ ወጣቶች