የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና ዘርፍ ምክር ቤት እና የነጋዴ ሴቶች ማህበር ምስረታ እየተካሄደ ይገኛል
ሀዋሳ፡ መጋቢት 02/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የንግድና ዘርፍ ምክር ቤት እና የነጋዴ ሴቶች ማህበር ምስረታ መድረክ በሀላባ ዞን ቁሊቶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ዳምጠዉ በምስረታ መድረኩ ማስጀመሪያ ላይ እንደተናገሩት፤ የንግድና ዘርፍ ም/ቤት እና የነጋዴ ሴቶች ማህበር በሸማችና አምራች መሀል ተዋናይ በመሆን በመካከላቸው የሚደረገውን የገበያ ትስስር ምቹ ስርዓት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ናቸዉ።
ምክር ቤቶቹ በትክክለኛዉ አሰራርና ስርዓት የሚንቀሳቀሱ ከሆነ እንደ ሀገር የተጋረጠውን የኑሮ ዉድነት ለማረጋጋት ሁሉም ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንዲሆን ሚናቸው የላቀ መሆኑን አመላክተዋል።
በምስረታ መድረኩ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ወይይት እየተደረገበት ሲሆን አዲስ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የንግድ ዘርፍ ም/ቤት ፕሬዝዳንት እና የነጋዴ ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ምርጫ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በመድረኩ የዞንና ልዩ ወረዳ የንግድና ገበያ ልማት ተቋማት ኃላፊዎች እና ነባር የንግድ ዘርፍ ፕሬዝዳንት እና የነጋዴ ሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት በመሳተፍ ላይ ናቸዉ።
ዘጋቢ፡ ብዙነሽ ዘዉዱ

More Stories
ብሔራዊ ምክክር ሀገራዊ አንድነትን ከማጠናከር ባሻገር ችግሮችን በውይይትና በሀሳብ የበላይነት ለመፍታት መሠረት እንደሚጥል ተገለጸ
የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 ጠቋሚ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው
የጠምባሮ ልዩ ወረዳ አርሶ አደሮች የመኸር እርሻ የማሳ ዝግጅት ቢያደርጉም በቂ ግብዓት አለማግኘታቸውን ገለጹ