በተዋረድ የሚገኙ የህዝብ ምክር ቤቶች አስፈላጊው ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ መጋቢት 02/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ምክር ቤቶች የተሠጣቸዉን የህዝብ ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ የአሪ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በዞኑ የምክር ቤቶች የጋራ ፎረም በጂንካ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የጂንካ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ወ/ሮ አበራሽ አበበ በዚህ ወቅት እንደገለጹት፥ የዞኑ ህዝብ የረጅም ጊዜ የመዋቅር ጥያቄ ምላሽ ባገኘበት ማግስት የተካሄደውን የምክር ቤቶች የጋራ ፎረም ልዩ እንደሚያደርገዉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫ እንደመሆናቸው መጠን ከሚያከናዉኗቸው ተግባራት አንዱ የጋራ ምክክር ፎረም መሆኑን የአሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡

አፈ ጉባዔዋ አያይዘውም በየደረጃው የምክር ቤቶችን አሠራር ለማጠናከርና አቅማቸዉን ለማጎልበት ፎረሙ ትልቅ ፋይዳ እንዳለዉ ተናግረዋል ፡፡

ምክር ቤቶች ህዝብን በመወከል የልማት ተደራሽነትን እውን ለማድረግ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን ተግባር መከታተልና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ሚናቸዉ እንዲወጡ ማድረግ እንደሚገባ የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ ገልፀዋል፡፡

በዞኑ በተዋረድ ያሉ ምክር ቤቶች የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን ዕቅድና አፈፃፀም በመገምገም የመንግስት የልማት ፖሊሲዎችን ተፈፃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚበረታታ እንደሆነም ዋና አስተዳዳሪው አክለዋል፡፡

ከፎርሙ በኋላም በጂንካ ከተማ አርክሻ ቀበሌ በከተማ ግብርና እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን የመስክ ምልከታ የተደረገ ሲሆን ቀጣዩን ፎረም የደቡብ አሪ ወረዳ እንደሚያዘጋጅ በመግለጽ ተጠናቋል፡፡

ዘጋቢ፡ በናወርቅ መንግስቱ – ከጂንካ ጣቢያችን