የዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ቀልጣፋ አለመሆን ለእንግልት እየዳረጋቸው መሆኑን ተገልጋዮች ተናገሩ

የዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት ቀልጣፋ አለመሆን ለእንግልት እየዳረጋቸው መሆኑን ተገልጋዮች ተናገሩ

ሀዋሳ፡ የካቲት 30/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የዲጂታል የትራንስፖርት አገልግሎት ቀልጣፋ አለመሆን ለእንግልት እየተዳረጉ መሆኑን በሚዛን መነኻሪያ ያገኘናቸው ተሳፋሪዎች ይናገራሉ።

ዘርፉ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ያሉ ጉድለቶች መኖራቸውን እና ጉድለቶች ለማረም እየተሰራ ነው ሲል የቤንች ሸኮ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ አስታውቋል።

የትራንስፖርቱን ዘርፍ ያዘመናሉ፣ ተሳፋሪውንም ከእንግልት እና ከተጨማሪ ወጪ ይታደጋል የተባለለት የዲጂታል ቲኬት አሰራር በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን በሚገኝ መነኻሪያ ከተጀመረ አምስት ወራትን አስቆጥሯል።

በመነኻሪው አገልግሎት ለማገኘት የመጡ ተሳፋሪዎች ዲጂታሉ በመነኻሪያ መጀመሩ ጥሩ ቢሆንም በተለይም በገበያ ቀናቶች ተሽከርካሪ በተገቢው ተሟልቶ አለመገኘት ከታርፍ በላይ መክፈል ሰልፍ መብዛት ዛሬም በትራንስፖርት ዘርፉ ያልተቀረፉ ችግሮች መሆናቸውን ተመላክቷል።

በመነኻሪያ የሚሰሩ አሽከርካሪዎችም ዲጂታሉ መምጣቱ ጥሩ ቢሆንም ካለው የተሳፋሪ ፍሰት አንጻር ተሽከርካሪ ተሟልቶ አለመቅረቡ ዲጂታል ማሽኑም ይሁን የሚሰሩ ባለሙያዎች ውስን መሆን ቀልጣፋ አሰራር አለመከተል ችግሮች ናቸው ይላሉ።

በመነኻሪያ የምእራብ ሶፍት ዌር ዲጂታል ስራ አስኪያጅ አቶ ጌዲዮን ማሞ በበኩላቸው ከህብረተሰቡም ይሁን ከአሽከርካሪዎች የሚነሱ ከሰው ኃይል እና ከዲጂታል ማሽን ጋር ያሉ እጥረቶች መኖራቸውን እና እሱን ለመፍታት እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

ከትራንስፖርት እጥረት ጋር ተሽከርካሪ እጥረት መኖር ሌላኛው ችግር በመሆኑ ተገልጋይ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዳያገኙ ምክንያት ነውም ብለዋል። ከትርፍ ክፍያ ጋር በተያያዘ  ባለሙያ መልስ ያለመስጠት ችግር መኖሩ ታውቆ እርምት እየተወሰደ ነውም ብለዋል።

የሚዛን አማን ከተማ የህዝብ ትራንስፖርት ዳይሪክተር አቶ ፊሊጶስ ቶማስ በበኩላቸው ከተሽከርካሪ እጥረት ጋር ተያይዞ በተለይም ማህበራቱ ተሽከርካሪዎችን አለማቅረብ ችግር ሲሆን 75 ያህል ተሽከርካሪዎች ስምሪት ውስጥ የሌላ መህናቸውን አንስተዋል።

ከዲጂታል ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች ዲጂታሉ በሚዛን መነኻሪያ ብቻ መኖሩ አለመስፋቱ  ተጨማሪ ሰው ከወንበር በላይ መጫን የባለሙያ እጥረት መኖር ለተሳፋሪ መልስ አለመስጠት  ችግሮች ሲሆኑ የተገኙ  ጥቅሞችም መኖራቸውንም ተናግረዋል።

በተለይም ስነምግባር የሌላቸው አሽከርካሪዎች ነፍሰጡር  ልጅ የያዙ እናቶችን እንዲሁም ወፋፍራም ሰወችን  የመንግስት ሰራተኛ አለመጫን  ሁኔታ የነበረው አሁን ተቀርፏልም ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን መንገድ ትራንስፖርት ልማት መምሪያ ምክትል መምሪያ ኃላፊ አቶ ዘለቀ ንጉሴ በበኩላቸው የዲጂታል ትራንስፖርት አገልግሎት በሚዛን አማን ከተማ ከተጀመረ አምስት ወራትን ያስቆጠ ሲሆን በአሰራሩ የተገኙ ውጤቶች እንዳሉ ሁሉ በጉድለት የሚነሱ ችገሮች መኖራቸውን እና እነሱን ለማረም ተገቢ ግምገማ በማድረግ የተሻለ አሰራር ተጠናክሮ ለማስቀጠል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘጋቢ:  አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን