የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ በሾኔ ከተማ የንፁህ መጠጥ  ውሃ የግንባታ ሂደት ተመለከቱ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ በሾኔ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ የግንባታ ሂደት ተመለከቱ

ሀዋሳ: የካቲት 30/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ በሀዲያ ዞን ሾኔ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ የግንባታ ሂደት ተመልክተዋል::

የሾኔ ንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በ2014 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን አሁን ላይ ግንባታው 83 በመቶ ላይ ይገኛል ተብሏል::

በሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮች ለክልሉ አመራር ገለፃ የተደረገ ሲሆን በቀጣይም ትኩረት ሰጥቶ በመሥራ ሊጠናቀቅ እንደሚገባ ተገልጿል::

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬን ጨምሮ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑሪዬ እና ሌሎችም የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች በምልከታው ተገኝተዋል::

ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ