ከሾኔ- አጀባ – ማዞሪያ ድረስ የተገነባው የጠጠር መንገድ ተመረቀ
ሀዋሳ: የካቲት 30/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን ዱራሜ ዲስትሪክት የተገነባው ከሾኔ- አጀባ – ማዞሪያ ድረስ የተገነባው የ18 ኪ.ሜ መንገድ የጠጠር መንገድ ተመርቋል::
በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ መንገዱን በይፋ አስመርቀዋል::
በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ በብልፅግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ጨምሮ በምክል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑሪዬ እና ሌሎችም የክልል እና የዞን የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል::
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ
More Stories
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
በእንስሳት እርባታ ከተሰማራን ወዲህ ኑሯችን ተሻሽሏል – የጋዘር ከተማ ወጣቶች