“ንባብ ለሁለናዊ ስኬት” በሚል መሪ ሃሳብ በታርጫ ከተማ የንባብ ሳምንት ፕሮግራም እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ፡ የካቲት 29/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) “ንባብ ለሁለናዊ ስኬት” በሚል መሪ ሃሳብ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ባህል ቱርዝምና ስፖርት ቢሮ በታርጫ ከተማ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የንባብ ሳምንት ፕሮግራም እየተካሄደ ነው::
በእለቱ ከኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤቴ-መፃህፍት አግልግሎት የንባብ ባህልን ለማዳበር እንዲቻል ከ 1 ነጥብ 3 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት የመፃሕፍት ድጋፍ ተደርጓል።
ንባብ ለሁንታናዊ እድገት በሚል መሪ ሃሳብ በታርጫ ከተማ በተካሄደዉ የኢትዮጵያ በቴ-መዛግብትና ቤተ-መፃህፍት አገልግሎት ኃላፊ አቶ አባተ ካሳ፥ ታርጫ ካሉት ከተለያዩ ት/ቤቶች የተወጣጡ ተማርዎችን ጨምሮ የተለያዩ የክልልና የዞኑ አመራሮች እንድሁም የተለያዩ አርትስቶች ተገኝተዋል።
የንባብ ባህልን ለማዳበር የክልሉ ባህል ቱርዝም ቢሮ ኃላፊ ተወካይና ምትክል ኃላፊ አቶ አክልሉ ለማ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዚህም ቢሮው የንባብ ባህልን ለማዳበር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ንባብ የሰዉን ልጅ በዘመናዊ መልኩ በመቅረጽ ረገድ ያለው ድርሻ የጎላ ነው ያሉት ኃላፊው፥ ሁሉም በእለቱ የተገኙት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የንባብ ባህልን በማዳበር ተምሳሌት መሆን እንዳለባቸዉም መልእክት ተላልፏል።
በዚህም በዞኑ ካሉት ወረዳዎች ለተወጣጡት 13 ት/ት የቤቶችና ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ግምታቸው ከ1 ነጥብ 3 ሚልዮን ብር በላይ የምሆን 4 ሺህ 5 መቶ 92 መፃሕፍት በስጦታ ተበርክቶላቸዋል።
ዘጋቢ፡ እሸቱ ወርቅነህ – ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
በዓሉ የብሔሮችና ብሔረሰቦችን ባህልና ፀጋዎች ለማስተዋወቅ የላቀ ሚና አለው
የቀቤና ልማት ማህበር (ቀልማ) የማህበረሰቡን ሁለትናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የያዛቸው ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አባላቱ ገለጹ
የፀረ ተህዋሲያን መድሃኒቶች መላመድ ለሰው ልጆች ስጋት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ