ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ) ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
ሀዋሳ፡ የካቲት 29/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር ) ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል፡፡
ለዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሴን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጣችሁም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ሀገራቱ ለቀጣይ ትብብር ጠንካራ መሰረት የሚሰጡ የረጅም ጊዜ ግንኙነቶችን የሚጋሩ መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ውይይታችን በርካታ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ ውጤታማ እንደነበርም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።
More Stories
ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች በኃላፊነት ሊሰሩ እንደሚገባ በጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ
የባስኬቶ ዞን ተወላጆች የአንድነት መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ነው
በእንስሳት እርባታ ከተሰማራን ወዲህ ኑሯችን ተሻሽሏል – የጋዘር ከተማ ወጣቶች