የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፌደራልና የክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች አባላት የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
ሀዋሳ: የካቲት 29/2016 ዓ.ም (ደሬቴድ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፌዴራል ፓርላማ እና የክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች አባላት ከወከሏቸው ህዝብ ጋር ያደረጉት ውይይት ግብረ-መልስ ማቅረቢያ መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው::
በውይይት መድረኩ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን ጨምሮ የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑሪዬ፣ ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና የሁለቱ ምክር ቤቶች የክልሉ ህዝብ ተወካዮች ተገኝተዋል::
ዘጋቢ፡ ማሬ ቃጦ
More Stories
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እያስመዘገበች ላለችው የዕድገት ጉዞ ቀጣይነት የትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለትምህርት ጥራት በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ሲል የጋሞ ዞን አስተዳደር አሳሰበ
በትምህርት ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን አጽንቶ ማስቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ ገለፁ
በኮንታ ዞን ጳጉሜን 1 – የጽናት ቀን በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል